ኦሮሚያ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ.

የዳይሬክተሮች ቦርድ አባልነት ዕጩዎችን ስለመጠቆም

የወጣ ማስታወቂያ

 

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መምሪያ ቁጥር SIB/42/2015 አንቀጽ 8 መሠረት በባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባዔ የተሰየመው የኦሮሚያ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ. የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት አስመራጭ ኮሚቴ (Election Committee) ሥራውን የጀመረ በመሆኑ በህግ የተቀመጡትን መስፈርቶች የሚያሟሉ የዕጩ ዳይሬክተሮች ጥቆማን ከኢንሹራንስ ኩባንያው ባለአክሲዮኖች ከሚያዚያ 1 ቀን 2009 ዓ.ም እስከ ሰኔ 30 ቀን 2009 ዓ.ም. ድረስ ይቀበላል፡፡

በብሔራዊ ባንክ መመሪያ ቁጥር SIB/32/2012 እናSIB/42/2015 መሰረት የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል ለመሆን የተቀመጡ መስፈርቶች እና ተጨማሪ መረጃዎች ፡-

 

1.   የኩባንያው ባለአክሲዮን የሆነ/የሆነች፣

2.   ዕድሜ ቢያንስ 30 ዓመት፣

3.   የትምህር ደረጃ፣

ሀ. ቢያንስ 75% የሚሆኑት የመጀመሪያ ዲግሪ ወይም ተመጣጣኝ የትምህርት ደረጃ ከታወቀ የትምህርት ተቋም ያላቸው፤

ለ. የቀሩት 25% ቢያንስ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ያጠናቀቁ መሆን አለባቸው፤

4.   የአስመራጭ ኮሚቴ አባል ያልሆነ/ች፣ የኩባንያው ወይም የሌላ መድን ሰጪ ኩባንያ ሠራተኛ ያልሆነ/ች፣

5.   የሥራ ልምድ፡- በህግ ፣ በመድህን፣ በምህንድስና ፣ በኢንቨስትመንት ማናጅመንት ፣ በአክቹዋሪያል ሳይንስ፣ በቢዝነስ ማናጅመንት፣ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፣ በአካውንቲንግ፣ በኦዲቲንግ፣ በፋይናንስ እና ሌሎች ተዛማጅነት ባላቸው ሙያዎች ላይ እና በቂ የሥራ ልምድ ያለው/ያላት መሆን አለባት/አለበት፣

6.   በሌላ የፋይናንስ ተቋም የቦርድ አባል ያልሆነ/ች፣

7.   የሕግ ሰውነት ያለው ድርጅት በዕጩነት ሊጠቆም ይችላል፣

8.   በኢትዮጵያና ከኢትዮጵያ ውጭ የእምነት ማጉደል ወይም የማጭበርበር ተግባር ያልፈፀመ/ች፣ ለፋይናንሻል ተቋማትና ለተቆጣጣሪ አካል ሐሰተኛ

መረጃ ያልሰጠ/ች፤ የሥነ-ምግባር ደንቦችን ባለማክበር የሥነ-ሥርዓት እርምጃ ያልተወሰደበት/ባት፤ በሙስና ወንጀል ተከሶ/ሳ ያልተፈረደበት/ባት

ከመምረጥና መመረጥ መብት ያልተገደበ/ች፤

9.   የፋይናንሻል ጤናማነትን (Financial Soundness) መስፈርት የሚያሟላ፤ ማለትም በኪሳራ ላይ ያልሆነ/ች፣ የታክስና የባንክ ግዴታዎቹን የተወጣ/ች፡፡

10  ከሚጠቆሙ 18 ዕጩዎች 1/3ኛው ማለትም ስድስት ዕጩዎች የሚጠቆሙት ከኢንሹራንስ ኩባንያው ጠቅላላ የተፈረመ ካፒታል 2% በታች ባላቸው (ተደማጭነት በሌላቸው - Non-Influential Shareholders) ባለአክሲዮኞች ብቻ ነው፤

11  ቀሪዎቹ 12 ወይም (2/3ኛ) ዕጩዎች ሁሉም ባለአክስዮኖች ከሚጠቁሙት ውስጥ ይሆናሉ፡፡

12  ማንኛውም ባለአክሲዮን ራሱን ወይም የህግ ሰውነት ያለውን ድርጅትን በመወከል ከተከታታይ ስድስት ዓመታት በላይ የቦርድ አባል ሆኖ ማገልገል አይችልም፤

13  ራሱን ወይም የሕግ ሰውነት ያለውን ድርጀት በመወከል ለስድስት ተከታታይ ዓመታት የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል በመሆን ያገለገለ ባለአክሲዮን እንደገና ለቦርድ አባልነት ሊጠቆም የሚችለው ከቦርድ አባልነቱ/ቷ ከተነሳ/ሳች በተከታታይ ስድስት ዓመት ካለፈ ብቻ ነው፤

14   ከላይ በተራ ቁጥር 10 እና 11 የተገለጸው ቢኖርም፣ የባለአክሲዮኞች ጠቅላላ ጉባዔው የዳይሬክተሮች ቦርድ ቀጣይነትን ለማረጋገጥ አስፈላጊ ነው ብሎ ካመነበት ከነባር ቦርድ አባላት በተከታታይ ከዘጠኝ ዓመታት በታች ያገለገሉትን ለአንድ የሥራ ዘመን (ለሦስት ዓመት) ብቻ እንደገና ለቦርድ አባልነት ሊመርጥ የሚችል ሲሆን፣ በዚህ አኳኋን የሚመረጡ የቦርድ አባለት ብዛት ከሦስት መብለጥ የለበትም፡፡

15  ከላይ የተጠቀሱት መመዘኛዎች እንደተጠበቁ ሆኖ ለዳይሬክተሮች ቦርድ ዕጩ አባልነት የሚጠቆም ማንኛውም ባለአክሲዮን በብሔራዊ ባንክ እና በባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባዔ እምነት የሚጣልበት/ባት፣ የኩባንያውን ዓላማዎቹ ለማሳካት በጎ ራዕይ ያለው/ያላት፣ ለመሥራት ፈቃደኛ እና ቁርጠኛ የሆነ/የሆነች፣ በጋራ አሰራር ሂደት ውስጥ ታማኝ፣ ሐቀኛ፣ የተሟላ ሰብዕና ያለው/ያላት መሆን አለበት/ባት፡፡

የኢንሹራንስ ኩባንያው ባለአክሲዮን የሆናችሁ የዕጩዎች ጥቆማ ቅፅን ሸዋ ዳቦ ፊት ለፊት፤ ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ ሕንፃ 6ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የዳይሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ ቢሮ ወይም ከሚቀርባችሁ የኩባንያው ቅርንጫፍ  ጽ/ቤት እንዲሁም ከኩባንያው ድረ-ገፅ  በመውሰድ ከላይ በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ የተቀመጠውን መስፈርት የሚያሟሉ የዳይሬክተሮች ቦርድ ዕጩዎችን መጠቆም የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፤ የተሞላውን ቅጽ በዋናው መ/ቤት፣ በቅርብ በሚገኘው የኩባንያው ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ወይም  በተመዘገበ የፖስታ ሣጥን ቁጥር መላክ የምትችሉ  መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ለበለጠ መረጃ በሚከተሉት አድራሻ በአስመራጭ ኮሚቴው ጽ/ቤት በኩል ማግኘት የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን፡፡

 

 

1.   በስልክ ቁጥር 0115 588122፣ በፋክስ ቁጥር 0115 588242

2.   በፖስታ ሳጥን ቁጥር 10090 አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ                  

3.     በኢ.ሜይል አድራሻ፡- oicelectioncommittee@gmail.com

 

 

የዳይሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ