kaampaanii Inshuraansii Oromiyaa W.A
ኦሮሚያ
ኢንሹራንስ ኩባንያ .

Oromia Insurance Company S.C

ማስታወቂያ

ለኦሮሚያ ኢንሹራንስ ኩባንያ . ባለአክሲዮኖች

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ ቁጥር SIB/42/2015 በሚደነግገው መሰረት በስምንተኛው የባለአክሲዮኖች መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ለሚካሄደው የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ምርጫ ዕጩ ዳይሬክተሮችን መልምሎ የሚያቀርብ  የዳይሬክተሮች አስመራጭ ኮሚቴ ሕዳር 6 ቀን 2009 ዓ.ም በተካሄደው የኦሮሚያ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ የባለአክሲዮኖች ሰባተኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ  መመረጡ ይታወቃል ፡፡

የዳይሬክተሮች አስመራጭ ኮሚቴው በቅድሚያ በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን ማስታወቂያ በማውጣትና የጥቆማ ቅፅ በሁሉም የኩባንያው ቅርንጫፎች በማሰራጨት ከሚያዚያ 1 ቀን 2009 ዓ.ም እስከ ሰኔ 30 ቀን 2009 ዓ.ም ድረስ የዕጩ ዳይሬክተሮችን ጥቆማ  ከባለ አክሲዮኖች ተቀብሏል፡፡ የዳይሬክተሮች አስመራጭ ኮሚቴው በመድን ሥራ አዋጅ ቁጥር 746/2004፣ በብሔራዊ ባንክ መመሪያዎች ቁጥር SIB/32/2012 እና SIB/42/2015፣ በኩባንያው የመመስረቻ ጽሁፍ እና መተዳደሪያ ደንብ፣ በዳይሬክተሮች ቦርድ የጥቆማና ምርጫ መመሪያ ፣ እንዲሁም አግባብነት ባላቸው የንግድ ሕግ ድንጋጌዎች ከተቀመጡ የብቃት መመዘኛዎች አከኋያ አስፈላጊውን የማጣራት ሥራዎችን ካደረገ በኋላ የሚከተሉትን ዕጩ ዳይሬክተሮች የመለመለ መሆኑንና ዕጩ ዳይሬክተሮቹ ለስምንተኛ የባለአክሲዮኖች መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ለምርጫ የሚቀርቡ መሆኑን  በአክብሮት ያስታውቃል ፡፡

              ለምርጫ የሚቀርቡ ዕጩ ዳይሬክተሮች

1.   አቶ. አለሙ ጢጣ ቢዶ                          10. አቶ. ደጀኔ ሂርጳ ቢሪ      

2.       አቶ. ዳዲ አሞሻ ቤኛ                       (የኦሮሚያ ቡና አምራች ገበሬዎች ህ/ስ/ዩኒየንን በመወከል)              

3.   አቶ. ሁንዱማ ግራኝ ሮሮ                        11. ኢ/ር አበራ በቀለ ወ/ሚካኤል

4.   አቶ. ለገሰ ታደሰ ቱሉ                           12. አቶ. ደጋ ጉርሜሳ ቶሌራ         

5.   አቶ. ግርማ ደለሳ ዳዲ                           13 አቶ. ታፈሰ ፋና ብሩ

  (የኦሮሚያ ደንና የዱር እንስሳት ድርጅትን በመወከል)  14. አቶ. ሰቦቃ ሙለታ ጅሬን

6.   አቶ. ፍቅሬ ሞያ ኩመላ                         15. አቶ በየነ በሊሳ አሙማ

7.   አቶ በየነ ጀልዱ አባጀበኔ                         16. አቶ ፍቅረዮሐንስ ያደሣ ፈይሣ

8.   አቶ. አቤ ሳኖ መሐመድ                         17. አቶ. አረጋ ጌላ ኤዱ

9.   አቶ ደመሳ ኡርጌሳ ቶሎሳ                        18 ወ/ሮ ማርታ ነመራ ወዬሣ

              በተጠባባቂነት የተያዙ ዕጩ ዳይሬክተሮች

1.   አቶ ዳባ ፈይሳ ሽፈራው                     3. ወ/ሮ ፌቨን ቀነዓ ቶርበን

2.   አቶ ጋሻው በንቲ ጉተማ                

ማሳሰቢያ፡-

§  ዕጩ ተወዳዳሪዎቹ ለዳይሬክተሮች ቦርድ አባልነት እንዳይወዳደሩና እንዳይመረጡ የሚያደርግ አግባብነት ያለው ማስረጃ ካላ የተከበራችሁ ባለአክሲዮኖች ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 የሥራ ቀናት ውስጥ ሸዋ ዳቦ ፊት ለፊት ፣ ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ ሕንፃ 6ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የዳይሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ ቢሮ በመቅረብ እንድታስታውቁ ኮሚቴው በአክብሮት ይጠይቃል ፡፡

ለበለጠ መረጃ ፡-በስልክ ቁጥር 0115 588122 ይደውሉ !

የዳይሬክተሮች አስመራጭ ኮሚቴ